የካዘን ባህሪያት
1.
ቀጣይነት ያለው
መሻሻል
የካይዘን ትግበራ ያልተካሄደባቸው
ቢዝነሶች ፤አምራች ድርጅቶች ምርትና ማሻሻያ
ቢኖራቸውም ቀጣይነት የለውም፡፡
በካይዘን የአመራር ፍልስፍና የታጀበ አሰራርን የሚያራምድ ድርጅት/ተቋም/ የምርት ጥራቱ፣ ምርታማነቱና አገልግሎት አሰጣጡ ቀጣይና
በማያቋርጥ ተከታታይ መሻሻል ሂደት ውስጥ ያልፋል፡፡
2.
ሁሉንም የሚያሳትፍ መሆኑ
ካይዘን ተግባራዊ በሚሆንበት
ድርጅት (ተቋም) ሁሉም ሰራተኛ ከማኔጅምንቱ እስከ ታች
ሰራተኛ መሳተፍ ይኖርበታል፡፡ የሁሉም ሰራተኞች ተሳትፎ ካልታከለበት ካይዘን
ተግባራዊ ሊሆን አይችልም፡፡
በካይዘን አተገባበር የማሻሻያ ሃሳብ ከከፍተኛ አመራር ደረጃ ወደ
ታች የሚመጣ ሳይሆን በዝቅተኛ
እርከን ከሚገኙ ሰራተኞች በማመንጨት ወደ ከፍተኛ
አመራሩ የሚቀርብ ይሆናል፡:በመሆኑም
የተጠናከረ የግንኙነትና ሃሳብን በነፃነት
የማቅረቢያ ስርዓትን መዘርጋት
ያስፈልጋል፡፡
3. ብዙ ወጪ የማይጠይቅ መሆኑ
·
ያለምንም ወጪ ወይም በትንሽ ወጪ ካይዘንን መተግበር ይቻላል፡፡
·
5ቱ ማዎችን በማስቀደም ሌሎች የካይዘን መሳሪያዎችን ለመተግበር የሚያስፈልገው የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡
·
የካይዘንን
ትግበራ ፅንሰ ሃሳብ ከግምት ውስጥ ያላስገባ የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት ብክነትን ያስከትላል
4. በሁሉም የዘርፍ ዓይነቶች የሚተገበር መሆኑ
በፋብሪካ፤በኢንተርፕራይዞች፤በህብረት ሰራ
ማህበራት፤አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፤በቢሮ፤በቤት፤
በቦርሳችንና በኪሳችንም
ሳይቀር ካይዘን ሊተገበር ይገባል፡፡
5. ትንንሽ
መሻሻሎች ድምር መሆኑ
ካይዘን በራሱ ትልቅ ውጤትን ለማምጣት ይችላል
በማለት የሚተገበር ሳይሆን በሚገኙ ጥቃቅን መሻሻሎች ጥርቅም ውጤት የሚፈልገውን ግዙፍ ለውጥ የሚያመጣ የአመራር ፍልስፍና
ነው፡፡
ካይዘን የትንንሽ መሻሻሎች ድምር ነው፡፡
የካይዘን ችግር አፈታት ዘዴ
mi
ReplyDelete