ካይዘን የጃፓን የአሰራር ፍልስፍና ሆኖ የአሰራር ልምዶችን፣ ብቃትን
ወዘተ በቀጣይነት ለማሻሻል የሚያስችል የአሰራር ፍልስፍና ነው፡፡
(ካይ): ለውጥ፣ መሻሻል
(ዘን): የተሻለ፣ መልካም፣ ጥሩ
|
ካይዘን - “የተሻለ ለውጥ”
- · ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው:፡
- · ካይዘን በምርት ሂደት ውስጥ የሚታዩ ብክነቶችን በማስወገድ ወይም በመቀነስ ያለንን ሀብት በቁጠባና እና አዋጭ በሆነ መንገድ ለመጠቀም በማስቻል ቀጣይና የማያቋርጥ የምርት ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል አሰራር ነው፡፡
- · ካይዘን ብክነትን በማስወገድ ጥራት፣ ወጪና የማስረከቢያጊዜያችንን በማሻሻል ቁልፍ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
- · ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው
- · ካይዘን ተከታታይ የሆነ የብቃት ዕድገት የሚያመጣ ስርዓት ሲሆን በተለይም በትኩረት ችግሮችን ከምንጫቸው እየለየና ምላሽ እየሰጠ የሚሄድ የለውጥ ስርዓት ነው፡፡
የካይዘን አስፈላጊነትና ጠቀሜታው
·
በምርት ሆነ በአገልሎት አሰጣጥ ወቅት ብክነትንና አላስፈላጊ
ወጪዎችን በመቀነስ፤ ሐብትን ከፍ የሚያደርግ ነው
·
ምቹ የስራ አካባቢን ይፈጥራል
·
የደንበኛ እርካታን ያሳድጋል
·
የድርጅቱን የተቋሙን ዘለቄታነት ያረጋግጣል
·
የማምረቻ ቦታችንን በአግባ እንድንጠቀም
ይረዳናል
·
ተከታታይ የሆነ ፈጣን ለውጦችን ያስገኛል
·
ተወዳዳሪነታችን እንዲጨምር ያደርጋል
·
የስራ እድል ይፈጥራል፤ የሐገርን
ገቢ ያሻሽላል
·
በምርት መምረት/ አገልግሎት አሰጣጥ
ወቅት እሴት የሚጨምሩ አሰራሮችን ያሻሽላል፡፡
·
የመረጃ ግንኙነትን በማጠናከር የአመራሩንና የሰራተኛውን ግንኙነት ያጠናክራል
No comments:
Post a Comment