Tuesday, March 10

የካዘን ባህሪያት


የካዘን ባህሪያት 


1.    ቀጣይነት ያለው መሻሻል

       የካይዘን ትግበራ ያልተካሄደባቸው ቢዝነሶች ፤አምራች ድርጅቶች ምርትና ማሻሻያ   

       ቢኖራቸውም ቀጣይነት የለውም፡፡ በካይዘን የአመራር ፍልስፍና የታጀበ አሰራርን የሚያራምድ ድርጅት/ተቋም/ የምርት ጥራቱ፣ ምርታማነቱና አገልግሎት አሰጣጡ ቀጣይና በማያቋርጥ ተከታታይ መሻሻል ሂደት ውስጥ ያልፋል፡፡  


2.  ሁሉንም የሚያሳትፍ መሆኑ
       ካይዘን ተግባራዊ በሚሆንበት ድርጅት (ተቋም) ሁሉም ሰራተኛ  ከማኔጅምንቱ እስከ ታች
       ሰራተኛ መሳተፍ ይኖርበታል፡፡ የሁሉም ሰራተኞች ተሳትፎ ካልታከለበት ካይዘን
      ተግባራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በካይዘን አተገባበር የማሻሻያ ሃሳብ ከከፍተኛ አመራር ደረጃ ወደ
       ታች የሚመጣ ሳይሆን በዝቅተኛ እርከን ከሚገኙ ሰራተኞች በማመንጨት ወደ ከፍተኛ
       አመራሩ የሚቀርብ ይሆናል፡:በመሆኑም የተጠናከረ የግንኙነትና ሃሳብን በነፃነት    
       የማቅረቢያ ስርዓትን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡



3.  ብዙ ወጪ የማይጠይቅ መሆኑ
·         ያለምንም ወጪ ወይም በትንሽ ወጪ ካይዘንን መተግበር ይቻላል፡፡
·         5 ማዎችን በማስቀደም ሌሎች የካይዘን መሳሪያዎችን ለመተግበር የሚያስፈልገው የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡
·         ካይዘንን ትግበራ ፅንሰ ሃሳብ ከግምት ውስጥ ያላስገባ የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት ብክነትን ያስከትላል
4.  በሁሉም የዘርፍ ዓይነቶች የሚተገበር መሆኑ
      በፋብሪካ፤በኢንተርፕራይዞች፤በህብረት ሰራ ማህበራት፤አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፤በቢሮ፤በቤት፤
     በቦርሳችንና በኪሳችንም ሳይቀር ካይዘን ሊተገበር ይገባል፡፡
5.  ትንንሽ  መሻሻሎች ድምር መሆኑ
       ካይዘን በራሱ ትልቅ ውጤትን ለማምጣት ይችላል በማለት የሚተገበር ሳይሆን በሚገኙ ጥቃቅን መሻሻሎች ጥርቅም ውጤት የሚፈልገውን ግዙፍ ለውጥ የሚያመጣ የአመራር ፍልስፍና ነው፡፡
ካይዘን የትንንሽ መሻሻሎች ድምር ነው፡፡




የካይዘን ችግር አፈታት ዘዴ
 




ካይዘን ምንድነው?



ካይዘን የጃፓን የአሰራር ፍልስፍና ሆኖ የአሰራር ዶች ቃትን ወዘተ ጣይነት ለማሻሻል የሚያስችል የአሰራር ፍልስፍና ነው፡፡
 (ካይ): ውጥ፣ ሻሻል
 (ዘን): የተሻለ፣ ልካ ጥሩ 
           
- የተሻለ ውጥ



  • ·        ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው:፡
  • ·   ካይዘን ርት ሂደት ውስጥ የሚታዩ ቶችን ገድ ወይም በነስ ብት እና ዋጭ በሆነ ንገድ ለመም በስቻል ይና ርጥ የርት ጥትና ርታማነትን ለማሳደግ የሚያስ አሰራር ነው፡፡
  • ·        ትን   ት፣   ስረጊዜያችንን ስተዋ
  • ·       ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው
  • ·       ካይዘን ተከታታይ የሆነ የብቃት ዕድገት የሚያመጣ ስርዓት ሲሆን በተለይም በትኩረት ችግሮችን ከምንጫቸው እየለየና ምላሽ እየሰጠ የሚሄድ የለውጥ ስርዓት ነው፡፡



የካይዘን አስፈላጊነትና ጠቀሜታው
·         በምርት ሆነ በአገልሎት አሰጣጥ ወቅት ብክነትንና አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ፤ ሐብትን ከፍ የሚያደርግ ነው

·         ምቹ የስራ አካባቢን ይፈጥራል

·         የደንበኛ እርካታን ያሳድጋል

·         የድርጅቱን የተቋሙን ዘለቄታነት ያረጋግጣል

·         የማምረቻ ቦታችንን በአግባ እንድንጠቀም ይረዳናል

·         ተከታታይ የሆነ ፈጣን ለውጦችን ያስገኛል

·         ተወዳዳሪነታችን እንዲጨምር ያደርጋል

·         የስራ እድል ይፈጥራል፤ የሐገርን ገቢ ያሻሽላል

·         በምርት መምረት/ አገልግሎት አሰጣጥ ወቅት እሴት የሚጨምሩ አሰራሮችን ያሻሽላል፡፡

·         የመረጃ ግንኙነትን በማጠናከር የአመራሩንና የሰራተኛውን ግንኙነት ያጠናክራል