ካይዘን እንደ ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች አንድ ጊዜ
ተተግብሮ የሚቆም ሳይሆን ሁል ጊዜ ሁሉም ቦታ ሊተገበር የሚችል የስራ አመራር ፍልስፍና ነው፡፡
·
ማቀድ(ማ)
·
መስራት(መ)
·
አፈጻጸምን መፈተሽና ማስተካከል(መፈ)
·
የተስተካከለውን ሃሳብ መተግበር(መተ)
ካይዘን እንደ ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች አንድ ጊዜ
ተተግብሮ የሚቆም ሳይሆን ሁል ጊዜ ሁሉም ቦታ ሊተገበር የሚችል የስራ አመራር ፍልስፍና ነው፡፡
·
ማቀድ(ማ)
·
መስራት(መ)
·
አፈጻጸምን መፈተሽና ማስተካከል(መፈ)
·
የተስተካከለውን ሃሳብ መተግበር(መተ)
ካይዘንን ለመተግበር ሚያስችሉ መሰረታዊ/አስፈላጊ አጀንዳዎች
1.
የስራ
ዕቅድ፡- የአጭርና የረጅም ጊዜ የምርት ወይም የአገልግሎት መስጠት ዕቅድ ለማዘጋጀትና ለመምራትም ሆነ
አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአመራር ችሎታ ነው፡፡
2. ወጪዎችን መመዝገብና የስራ መረጃዎችን መያዝ፡-በካይዘን
ትግበራ የአንድን ነጠላ ምርት ወጪ መረጃ በጣም ወሳኙና አስፈላጊ ነው፡፡ይህ ወቅታዊ የሆኑ የምርት ወይም የአገልግሎት ወጪን ለመተንተን
ብቻ ሳይሆን በካይዘን ትግበራ ወቅት ለማሻሻል ከምናስቀምጠው ግብና የሚገኘውን ውጤት ከምርት ወይም ከአገልግሎት ወጪ
አንፃር ለመለካት ያስችላል፡፡ በተጨማሪ የተለያዩ የስራ መረጃዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡የስራ መረጃዎች ከተለያዩ የስራ አመላካቾች
ጋር የሚገናኙና ለምርት፤ለአገልግሎት ጥራት፤ለምርት ማስረከቢያ ጊዜ፤ለስራ ላይ ደህንነትና ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት
የሚፈጅበትን ሰዓት፤የተፈጠሩ የምርት ግድፈቶች፤ የአገልግሎት ቅሬታዎችና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
3. እምነትና ኃላፊነትን መስጠት፡- ካይዘን
በከፍተኛ አመራር፤ በመካከለኛ አመራርና ለስራው ቅርብ በሆኑ ሰራተኞች ቅንጅት የሚተገበር ነው፡፡ ስለዚህ እምነትና ኃላፊነትን መስጠት
የካይዘን አመራር ፍልስፍና ሲሆን፤
·
ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት መደገፍ
·
አስፈላጊውን ኃላፊነት ለአመራር/ሱፐርቫይዘሮች መስጠት
·
ለሰራተኞች የስልጠና ዕድል ማመቻቸትና ሰራተኛን ማመን ያስፈልጋል
የካይዘን
ህግ/ደንብ
·
ለደንበኛ ትኩረት መስጠቱ፤
·
ቀጣይና የማያቋርጥ መሻሻል ማምጣቱ፤
·
ችግሮችን የሚያሳውቅ መሆኑ፤
·
የስራ ቡድኖችን ሚፈጥር መሆኑ
·
የተለያየ ዕውቀት ያላቸውን ቡድኖች ውስጥሚካተት መሆኑ፤
·
ትክክለኛ ሂደትን የሚከተል መሆኑ፤
·
ራስን መግዛት ማሳደጉ፤
·
እያንዳንዱ ሰራተኛ መረጃ እንዲያገኝ ማድረጉ
·
እያንዳንዱ ሰራተኛ አስፈላጊውን ስልጠና
እንዲያገኝ የሚያደርግ መሆኑ
ካይዘን
ለመተግበር ምን ያስፈልጋል
·
የካይዘን ዕውቀት
·
ቀና አስተሳሰብ
·
የሁሉም ተሳትፎ
·
ፍላጎትና ድጋፍ
·
ስለ ካይዘን ማስተማርና መማር
·
ካይዘን በቀጣይነት መተግበር
ሊተኮርባቸው
የሚገባቸው ጉዳዮች
1. ጥራት
ጥራት
ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ለመጠቀም ተስማሚ ሆኖ ሲቀርብ ነው፡፡ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ የደንበኛን አጠቃላይ ፍላጎት
ማሟላት የሚኖርበት ሲሆን የጥራት ቁጥጥርና የደንበኛ ቅሬታ የአንድን ምርት ወይም አገልግሎት ጥራት የሚወስኑ ናቸው፡፡
2. ወጪ
ወጪ ማለት
አንድን ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የምናወጣው የግብዓት፤ሰው ኃይል፤የመሳሪያና ሌሎች ወጪዎች ማለት ነው፡፡ የአንድ
ዕቃ ዋጋ የሚወሰነው በወጪ መርህ ሳይሆን በገበያ ፍላጎት መሆን ይኖርበታል፡፡
·
በተለምዶአዊ
ወይም በወጪ መርህ ዋጋ የሚወሰነው ፡- ዋጋ = ወጪ + ትርፍ
·
በገበያ
መርህ ወይም በካይዘን ዋጋ የሚወሰነው ፡- ትርፍ
= ዋጋ - ወጪ ነው፡፡
|
3.
ምርታማነት
ምርታማነት
ማለት አንድን ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት
ሚያስፈልጉትን እንደ ግብዓት፤የሰው ኃይል፤መሳሪያና ሌሎች ወጪዎች
በተቻለ
መጠን በዝቅተኛ ወጪ ከፍተኛ ምርት ወይም አገልግሎት ማግኘት
ነው፡
1. የማቅረቢያ ጊዜ
የማቅረቢያ ጊዜ ማለት አንድን
ምርት አምርቶ ለደንበኛ ማስረከብ የሚቻልበት
ጊዜ ነው፡፡
2.
የስራ ቦታ ደህንነት
ምርት
ወይም አገልግሎት በሚሰጥበት አካባቢ የሠራተኛውን ደህንነት
የሚጎዱትን ዕቃዎች ወይም አሰራሮች ማስተካከል ነው፡፡
3. የስራ ተነሳሽነት
ሰራተኛው
ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በተለየ ምርትን በጥራት በማምረት
ወይም አገልግሎትን በተሸለ መንገድ ለመስጠት ሲነሳ ነው፡፡
4.
አካባቢያችን - የውሃ አጠቃቀም፣ የአየር መበከል፣ የድምጽ ሁኔታ፣ተረፈ
ምርት……